Search results for - adama
-
-
-
-
ኦሊጅ ሮዝስ ኤትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ
P.O. Box 1587ኦሊጅ ሮዝስ ተቆርጠው የተዘጋጁና በሽክላ የተተከሉ ፅጌሬዳዎችን በማዳቀል፣በማፍላት እና በመሸጥ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ተቆርጠው በሚቀርቡ ፅጌሬዳ አበቦች ላይ ከ10 ዓመታት በላይ ልምድ አለው::ማለትም እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ከ1980 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ተቆርጠው የሚቀርቡ ፅጌሬዳዎችን ያቀርብ የነበረ ሲሆን ከ2004 ጀምሮ ደግሞ በሸክላ ላይ ተተክለው የሚበቅሉ አበቦችን ለገበያ አቅርቧል::
-
-
ኦሮሚያ ግብርና ቢሮ
P.O.Box 8770 Finfinne/ Addis Ababa, Ethiopiaዘመናዊ የግብርና ገበያ ለመፍጠር ዘላቂ ገቢ ያረጋግጣል
-
-
የኦሮሚያ ክልል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
የኦሮሚያ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 71/95 የተቋቋመ ሲሆን፣ ራዕይ በ2012 ዓ.ም ሙስናና ብልሹ አሠራር በኦሮሚያ ክልል ዕድገትና መልካም አስተዳደር ላይ እንቅፋት ከማይሆንበት ደረጃ ላይ ማድረስ፣ ተልዕኮ • የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርትን በማስፋፋት የነቃና ሙስናና ብልሹ አሠራርን የማይሸከም ህብረተሰብ መፍጠር፣ • በክልሉ የመንግሥት መ/ቤቶችና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጡና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሠራር ሥርዓቶችን በማጥናትና ለሙስና በር የሚከፍቱ ቀዳዳዎችን አስቀድሞ በመዝጋት ሙስናን መከላከል፣ • ተሾሚዎች፣ተመራጮችና በህግ ሀብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ የተጣለባቸውን የመንግስት ሠራተኞችን ሀብትና የገንዘብ ጥቅሞች መዝግቦ የመያዝ ወይም ተመዝግቦ እንዲያዙ ማድረግ፣ • በክልሉ የመንግስት መ/ቤቶችና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ከባድ የሥነ-ምግባር ጥሰት ስለመፈፀሙ ጥቆማ ሲደርሰው ወይም በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው በመመርመርና በመክሰስ ለህግ በማቅረብ፤እንዲሁም በሙስና ወንጀል የተመዘበረውን የህዝብ ሀብት ወይም ንብረት በማስወረስ ለሕዝብና ለመንግስት ጥቅም እንዲውል ማድረግ ናቸው፡፡ የኮሚሽኑ የትኩረት አቅጣጫዎች ሙስና የፈርጀ ብዙ ችግሮች መንስኤ ከመሆኑ የተነሣ የፀረ-ሙስና ትግሉም የተለያዩ የትኩረት አቅጣጫዎችን ከተከተለ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል፡፡ ሙስና ሀገሪቱ እየተገበረችው ላለው የሠላም የልማትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት እንዳይሆን ኮሚሽናችን አራት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ነድፎ በትጋት በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ የትኩረት አቅጣጫዎችም፡- 1. በመንግሥት የገቢ ግብር አሰባሰብና አስተዳደር ዙሪያ፣ 2. በመንግስት ትላልቅ ግዢዎች ዙሪያ፣ 3. በከተሞች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ፣ 4. በፍትህ ሥርዓት ዙሪያ የሚታዩ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ማዕከል ያደረገ ይሆናል፡፡
-
-