ራዕይ
በ2020ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በማደስ አዋጭና ውጤታማ የመሬት ዝግጅት በማከናወን የተሸሻለ የስራና የመኖሪያ አካባቢ በመፍጠር የከተማዋን ልማት እንዲፋጠን በማደረግ አዲስ አበባን አዲስ ማድረግ፡፡
የኤጀንሲዉ ተግባርና ኃላፊነት
1.በከተማዋ ክልል ውስጥ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች የሚውል መሬት ያዘጋጃል፡፡
2.በህዝብ ተሣትፎ የሚለማው እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማዋ የተጎዱና የደቀቁ አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት ሥራ ያለማል፤ያድሳል፡፡
3. ከተማው ውስጥ በልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችና መልሶ ማልማት ተነሺ ለሆኑት ተገቢውን የካሳ ግምት ይተምናል፤ የካሣ ክፍያ ይፈፅማል፤ ምትክ ቦታ ያዘጋጃል፤
4. በመልሶ ማልማትና ለመሬት ዝግጅት ተፈላጊዉን መሠረተ ልማት ያጠናል፤ ለሚመለከታቸዉ ያሳዉቃል፤ ከገንቢዎች በሚገኝ ግብአት የግንባታ ቅንጅት ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም ያስገነባል፡፡
አዋጅ ቁጥር 455/1997 መሰረት የካሳና የምትክ እና የልማት ተነሺ መብትና ግዴታ በተደነገገዉ መሰረት ይፈፀማል፤ ደንብቁጥር 135/1999፤ የካሳ መመሪያ ቁጥር 19/2006 መሰረት ቅድመ ሁኔታዎች፤ መብቶች፤ ግዴታዎች፤ ክልከላዎች በግልፅ የተደነገገዉን አሳታፊነትን እና ህብረተሰብ ተኮርና ልማት ተነሺን ተጠቃሚ ያደረገ እንዲሁም ተጠቃሚነትን መተግበር የሚያስችል አሰራርን የተከተለ ነዉ፡፡
የመልሶ ማልማት ሊካሄድባቸው የሚችሉትን የከተማዋን መሃል አካባቢዎች በመለየትና የአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) በመስራት፣ ተነሺዎችን በተደጋጋሚ በማወያየትና በማሳመን፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ የምትክ ቦታ/ቤት አሰጣጥ እና የካሳ አከፋፈል ሥርዓትን በማስፈን በልደታ፣ በሰንጋተራ፣ በአራትኪሎ ባሻወልዴ፣ በፓርላማና በሌሎችም አካባቢዎች በጥቅሉ ከ360.12 ሄ.ር በላይ በሆነ መሬት ላይ የተለያዩ የመልሶ ማልማት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከ20ሺ በላይ የልማት ተነሺዎችን በማስነሳት1.01 ቢሊየን ብር ካሳ በመክፈል ለ1,600 ተነሽዎች የማቋቋሚያ ድጋፍ የተሰጠ ሲሆን በሌላ መልኩ በመጀመሪያ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከ2006-2009 በጅት አመት ለተለያዬ አገልግሎት የሚውል የተዘጋጁ መሬቶች 5924.693 ሄ/ር መሬት ማዘጋጀት ተችሏል::