ጀንትል ሆቴል
የክፍል ሽያጭና የምግብና መጠጥ እንዲሁም የግብዛ አገልግሎት ስራ
የክፍል ሽያጭና የምግብና መጠጥ እንዲሁም የግብዛ አገልግሎት ስራ
የህትመት አገልግሎት እና የሰውሃይ የማቅረብ አገልግሎት እንሰጣለን።
ጂነስ ግሎባል ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ.
ጂኦ ማርክ ሲስተም ኃ.የተ.የግ.ማ
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ የተለያዩ የሥነምድር ጥናት ዘዴዎችን በመጠቀም በማዕድን ምርመራ ልማት ሥራዎች ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች በተተለያዩ ዘርፎች የልማት ፕሮጀክቶችን ለማካሄድ፤ ለመሰረተልማትና ለኢንዱስትሪ ልማት በግብርና ልማት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ መሰረታዊ የጂኦሳይንስ መረጃ ጥናት በማመንጨትና ለተጠቃሚዎች በማሰራጨት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የበኩሉ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ሰርቬዩ እስካሁን ባካሄዳቸው ጥናቶች ለኢንቨስትመንት የተዘጋጁ የተለያዩ የማዕድን አለኝታ መጠን እና የሚገኙበትን ቦታ በካርታ አዘጋጅቷል፡፡ ለምሳሌ ያህል ከብረትና ብረት ነክ ማዕድናት መካከል እንደ ወርቅ፣ ታንታለም፣ ፕላቲኒየም፣ መዳብ፣ ብረትና ሌሎች በርካታ ማዕድናት፣ ከኢንዱስትሪ ማዕድናት መካከል እንደ ኖራ ድንጋይ፣ ፑሚስ፣ ጀሶ፣ ፖታሽ፣ ፎስፌት፣ እምነበረድ እና ሌሎች ማዕድናት እንዲሁም ለሀይል ምንጭነት አገልግሎት የሚውሉ እንደ ድንጋይ ከሠል፣ ኦይል ሼል፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የተፈጥሮ ዘይት፣ የጂኦተርማል ሀብትና በርካታ የኮንስትራክሽን ማዕድናት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለያየ መጠን እንደሚገኙ በማረጋገጥ መረጃውን በካርታ አዘጋጀቶ ተጠቃሚዎችን እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ሰርቬዩ በዘርፉ ለተሠማሩና ለሚሠማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለምርምርና ለስልጠና ተቋሞች እንዲሁም የመሠረተ ልማት ሥራዎች የተለያዩ የቁፋሮ፣ የሥነምድር ናሙና ምርመራ፣ ልዩልዩ የማማከር አገልግሎቶችን እንዲሁም የሥነ-ምድር መረጃ አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሠጣል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ ለተሠማራችሁ እና ለመሰማራት ለምትፈልጉ ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለምትፈልጉ የግል ባለሀብቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆናችሁ ድርጅቶች፣ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሰርቬዩ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡