MILLSTONE ADVERTISING PLC
ሚሊስቶን አድቨርታይዚንግ ኤጀንሲ ኃ.የተ.የግ.ማ
ሚሊስቶን አድቨርታይዚንግ ኤጀንሲ ኃ.የተ.የግ.ማ
ዓላማ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለአገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን ወሳኝ የሆኑ መሰረተ-ልማቶችን የማስፋፋት ተልዕኮውን በብቃት መወጣት የሚችል፣ ከሌሎች የምርትና አገልግሎት ዘርፎች ጋር የጠበቀ ትስስር ያለውና በዓለም አቀፍ ደረጃ የመወዳደር አቅም እየገነባ በቀጣይነት እንዲያድግ ማድረግ ነው፡፡ ራዕይ በ2017 አገራዊው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የማስፈፀም አቅም አድጎ እና የአገር ውስጥ የገበያ ፍላጎትን አሟልቶ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ማየት ነው፡፡ ተልዕኮ የዘርፉን ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት በማስተባበርና በማቀናጀት ደረጃውን የጠበቀና ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመገንባት አገራዊ የልማት ራዕይን ዕውን ማድረግ ነው፡፡ እሴቶች፡- . ሀቀኝነት፣ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት፣ . የአሠራር መርህን ተከትሎ መስራት፣ . ለውጤታማነትና ለቅልጥፍና ዘወትር መትጋት፣ . ሁሌም በማያቋርጥ የመማርና የመማማር ሂደት ላይ መሆን፣ . ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት፣ . ሁሉን ሰው እኩል ማየትና . የተለያዩ ሃሳቦችን በአግባቡ ማስተናገድ ናቸው፡፡
በአገሪቱ በፍጥነት እያደገ ባለው ኢኮኖሚ ውስጥ ጥሩ ችሎታ እና ብቃት ያለው የተማረ የሰው ሃይል ማፍራት፡፡
ራዕይ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ የተመጣጠነ ልማትና የተጠናከረ የመንግሥታት ግንኙነት በ2017 እውን ሆኖ ማየት፣ ተልዕኮ የፌዴራል አካላት እገዛን በማስተባበርና በማቀናጀት ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች እና በአርብቶ አደር አካባቢዎች ተመጣጣኝ ልማት ማረጋገጥ፣ የግጭት መከላከልና አፈታት ስርዓት በመዘርጋት፣ በተለያዩ የሐይማኖትና እምነት ተቋማትና ተከታዮች መካከል ያለውን መልካም ግንኙነቶች በማዳበር፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነትን በመከላከልና በመቆጣጠር የሕዝቡን ሠላም ማረጋገጥ፣ በፌዴራል መንግስትና በክልሎች መካከል የግንኙነቶች ማእከል ሆኖ በማገልገል የፌዴራል ሥርዓቱን ማጠናከር ፡፡
ሀገራዊ ራዕይ በህዝብ ተሳትፎና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ